የአፋር ልማት ማህበር ከክልሉ ከፍተኛ ፣ መካከለኛ እና ዞን ወረዳ አመራሮች ጋር የስድስት ወር አፈጻጸም ሪፖርት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ በሰመራ ከተማ እያካሄደ ይገኛል
በዚሁ ውይይት መድረክ ላይ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንትና መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ሀላፊ አቶ ኡመር ኑር የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ዞንና ወረዳ አመራሮችና በለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። በዚሁ ውይይት መድረክ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንትና መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ሀላፊ አቶ ኡመር ኑር እንደተናገሩት የአፋር ልማት ማህበር የአፋር ህዝብ ችግር በተለያዩ ዘርፍ እየቀረፈ የመጣ ማህበር ነው:: ልማት ማህበሩ በቀጣይ የሚያከናውኑት ተግባራት ስኬታማነት የሁሉም ባለድርሻ አካለት እርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን ገልጿል::






